በኮርና ቫይረስ ምክንያት የቢቱዋህ ሌኡሚ አጠቃላይ መመሪያዎች፦
ያለክፍያ ለዕረፍት የወጡ ቋሚ ሰራተኞች ወይንም ስራቸው ለተቋረጠባቸው ሰራተኞች የሚሰጥ የገንዘብ ክፍያ፦
አንድ ሰራተኛ ለ 30 ቀናት ወይም ከዚያ በላይ ያለ ክፍያ ለዕረፍ ከወጣ ወይም ሥራው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ያለፍላጎቱ (ከሥራ መባረሩ ፣ የሸፍት መቋረጥ) ከተቋረጠ ከቢቱዋህ ሌኡሚ የገንዘብ ክፍያ የመቀበል መብት አለው፡፡
አንድ ሰራተኛ ስራው ከተቀነሰ ወይንም ለሁለት ሳምንት ያህል በባይረሱ ምክንያት ብቻውን መቆየት ያለበት ሰራተኛ፤ በስራ አጥነት የሚሰጠውን የገንዘብ ክፍያ መቀብል አይችልም፡፡
ያለ ክፍያ ለዕረፍት የወጡ ሰራተኞች ማስተዋል የሚያስፈልጋቸው ነገር፦ ይህ የገንዘብ ክፍያ የሚሰጣችሁ ለዕረፍት ከወጣችሁበት ቀን አንስቶ ሲሆን፤ የሚሰጣችሁን ዓመታዊ የዕረፍት ቀናት ባትጠቀሙም እንኳ ክፍያውን መቀበል ትችላላችሁ፡፡
- አንድ ሰራተኛ ከ 1.3.20 ቀን በኋላ የስራ አጥነት ቀናቱ ካበቃበት፤ እስከ 30.4.20 ቀን ድረስ እኛ እናራዝምለታለን፡፡
- ካለፉት 18 ወራት ውሥጥ ቢያንስ 6 ወር ከሰራ (በ 12 ፈንታ)
ስለግማሹየሥራአጥነትቀናትየገንዘብክፍያውንይቀበላል፡፡
የሥራ አጥነትን ክፍያ ለመቀበል የሚያስፈልጉ ቅደም ተከተሎች፦
- በሥራ ስምሪት አገልግሎት ውስጥ ምዝገባ - የሥራ አጥነት ክፍያ ለመቀበል ስራዎን እንዳቆሙ ወዲያውን በስራ ሥምሪት አገልግሎት መመዝገብ አለብዎት -
በስራሥምሪትአገልግሎትድህ_ገፅ መመዝገቢያ
በስራ ስምሪት አገልግሎት እስከ 26.3.2020 ድረስ የሚመዘገብ፤ በ 15.3.2020 እንደተመዘገበ ይቆጠርለታል፡፡
ከተመዘገቡ በኋላ፤ በስራ ሥምሪት አገልግሎት ማዕከላት በአካል መገኘት እንዳለብዎት የሥራ ስምሪት የሚያወጣቸውን መመሪያዎች መከታተል አለብዎት፡፡
-
የስራ አጥነት ክፍያ ከቢቱዋህ ሌኡሚ ማመልከቻ፦ በቢቱዋህ ሌኡሚ ድህረ ገፅ ማመልከቻውን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ማመልከቻዋን ለማቅረብ ከዚህ ይጫኑ፡፡
ማመልከቻውን ለማቅረብ ግዴታ ከቢቱዋህ ሌኡሚ ድርጀት መምጣት አያስፈልግዎትም፡፡
ከማመልከቻው ጋር መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች፦
የአሰሪውን የቅጥር ጊዜ እና ደመወዝ ማፅደቅ(በለ/1514)_ ከፍቃዱ ላይ አሰሪ ያለ ክፍያ ለዕረፍት መውጣት የወሰነው(የጠየቀው) ማን እንደሆነ፤ ያለ ክፍያ ሰራተኛው ለዕረፍት የወጣበት ቀን፤ ያለ ክፍያ ዕረፍት ለሥንት ጊዜ እንደሆነ መግለጥፅ አለበት፡፡
በግል የአገልግሎት ጣቢያዎ ላይ የማመልከቻዎ ጉዳይ የት እንደደረሰ መከታተል ይችላሉ፡፡
ማመልከቻዎ ከጥቂት ቀናት በኋላ በድህ_ገፁ ይታያል። ስለዚህ የጉዳይዎ ሁኔታ ምን ደርጃ ላይ እንዳለ መመልከት፣ የላክንልልዎትን ደብዳቤዎች እና ሌሎችን በግል አገልግሎት ጣቢያ መምልከት ይችላሉ፡፡
የሥራ አጥነት ክፍያ መጠን፦
በቀላል መንገድ እና በፍጥነት የሚሰጠዎን ክፍያ በደመወዝዎ መሰረት ስሌት ለማድረግ፤
በስራአጥነትየስራክፍያማስያ መጥቀምይቻላሉ፡፡
ስለክፍያመጠንለተጨማሪመረጃከዚህይጫኑ
የሥራ አጥነት ክፍያ የጊዜ ገደብ
የሥራ አጥነት ክፍያ የቀን ብዛት በእድሜ እና በቤተሰብ መጠን ይለያያል፦
ለበለጠመረጃከዚህየመገናኛመርብይግቡ፡፡
በዚህ የሥራ አጥነት በሚቆይበት ጊዜ ከስራ ስምሪት አገልግሎት ለሚሰጠዎት የስራ አማራጭ ዝግጁ ሆነው መገኘት አለበዎት፡፡ እንዲሁም እንደ ማንኛውም ሥራ ፈላጊ ሰው የስራ ስምሪት አገልግሎት በወሰነልዎት ቀን እና ሥዓት መገኘት አለብዎት፡፡
በሥራ አጥነት ምክንያት ክፍያ እየተቀበሉ ባሉበት ወቅት ያልተለመደ የስራ አቅራቦት ቢያገኙ እና ስራውን ከሰሩ - ለቢቱዋህ ሌኡሚ ወይም ለሥራ ስምሪት አገልግሎት የሥልጠና ቀናትን (ስራ አጥ እንዳልሆኑ) የማሳወቅ ግዴታ አለብዎት፡፡ ለቢቱዋህ ሌኡሚ ካሳወቁ - ከሚያገኙት አጠቃላይ የሥራ አጥነት ክፍያ መጠን ይቀነሳል፡፡ እንዲሁም ለስራ ስምሪት አገልግሎት ካስታወቁ - ሥራ በሰሩባቸው ቀናት ስራ ፈላጊ እንዳልሆኑ እንዳይመዘግብዎት ያሥረዱ፡፡
ለማን ነው የሚያመለክቱት?
ምዝገባ እና በሥራ ስምሪት ማዕከል መገኘትን በተመለከተ ለሚነሱ ማንኛውም ጥያቄ ለስራ ሥምሪት አገልግሎት ያመልክቱ፡፡
ማመልከቻ ማስገባት በተመለከተ ለሚነሱ ማንኛውም ጥያቄዎች በሚቀጥለው ስልክ ቁጥር ሊደዉሉልን ይችላሉ፦ *6050 ወይንም በድህረ_ገፃችንማመልከቻዎንለእርስዎቅርንጫይልኩ፡፡
የብቃት ምዘና ወራት ወደ 6 ማሳጠር
የኮሮና ቫይረስን ቀውስ ተከትሎ፤ ከ 1.3.2020 እስከ 19.4.2020 ያለ ክፍያ ዕረፍት መውሰድ ከተገደዱ ወይም ከሥራ ከተባረሩ እና ካለፉት 18 ወራት ውስጥ ቢያንስ 6 ወራት ሥራ ከሰሩ(ለ 12 ወራት ያህል ከሰራ ሰው ጋር ሲነፃፀር)፤ ስለግማሹ የሥራ አጥነት ቀናት የገንዘብ ክፍያውን ይቀበላሉ፡፡
የስራ አጥነት ክፍያ ለስንት ቀናት ማግኘት ይቻላል?
የሥራ አጥነት ክፍያ የሚያገኙበት ከፍተኛ የቀን ብዛት በእድሜዎ እና ከእርስዎ ጋር ከሚኖሩት ሰዎች (ወንድ የትዳር ጓደኛ ፣ ሴት የትዳር ጓደኛ ፣ ልጅ) ብዛት መሰረት የወሰናል፡፡
በጣም ማወቅ የሚያስፈልገው ነገር፦ ለስራ አጥነት ከፍተኛ የክፍያ ቀናት ብቁ የሚሆኑበት ሁኔታ በእድሜዎ ላይ በሚታዩ ለውጦች ወይም ከእርስዎ ጋር በሚኖሩት ሰዎች ቁጥር ብዛት በመመርኮዝ ይወሰናል፡፡
የዕድሜ ቡድን |
ከ 3 በላይ ሰዎች አብረውት የሚኖሩ ከሆነ |
ከ 2 በላይ ሰዎች አብረውት የሚኖሩ ከሆነ |
---|
እስከ 25 |
69 ቀናት | 25 ቀናት |
25 እስከ 28 |
69 ቀናት | 34 ቀናት |
28 እስከ 35 |
69 ቀናት | 50 ቀናት |
35 እስከ 45 |
87 ቀናት |
69 ቀናት |
45 እና ከዚያ በላይ |
87 ቀናት |
87 ቀናት |
መታወቅ ያለበት አስፈላጊ ነገር፦
ከሚሰሩበት ቦታ 6 ወራት ካልሰሩ - ለስራ ወራት የማይቆጠሩ ወራት እና ለብቃት ምዘና ጊዜ ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉ ተጨማሪ የስራ ወራት አሉ -
ለተጨማሪመረጃከዚህይጫኑ፡፡
ያስተውሉ፦ ግዴታዊ የወትድርና አገልግሎት ያጠናቀቁ ወታደሮች እና ሽሩት ሌኡሚ / የዜጎች በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ያጠናቀቁ ወጣቶች፤ በስልጠና ጊዜ የአገልግሎቱ ወራት እንደማየካተቱ እባክዎ ልብ ይበሉ፡፡
እድሜያቸው ለጡረታ ለደረሰ አዛውንት መረጃ:-
የሥራ አጥነት ክፍያ የሚሰጠው የጡረታ ዕድሜ እስከሚደርስ ነው፡፡ ይህ ማለትም፦ እስከ 67 ዓመት ድረስ ይሆናል፡፡
ማንኛውም ሰው እድሜው ከ 67 ዓመት በላይ (ሴቶችንና ወንዶችን) ከሆነ እና ስራ መስራት ያቋረጠ/ችው በኮሮና ቫይረስ ቀውስ ምክንያት ከሆነ፤ ለአዛውንትዜጋየሚሰጠውንክፍያ እንዲያገኝ መጠየቅ ያስፈልገዋል፡፡ እንዲሁም ገቢው ዝቅተኛ ከሆነ፤ ለአዛውንት ዜጋ አበል
ለተጨማሪየገቢመደጎሚያ ማመልከቻ ማቅረብ ይችላል፡፡
እድሜያቸው ከ 62 እስከ 67 ዓመት የሆኑ ሴቶች ለአረጋዊያን ወይም ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁ ናቸው - ከሁለቱ ከፍያዎች ከፍ ያለውን ክፍያ ይቀበላሉ፡፡ ስለዚህ ለሁለቱ ክፍያዎች ማመልካቻ ማስገባት መልካም ሲሆን፤ እኛም ከፍ ያለውን ክፍያ እንዲቀበሉ እናደርጋለን፡፡
እድሜያቸው 67 ዓመት በላይ ለሆነ የሚሰጥ የእርዳታ ክፍያ፦
በኮሮና ቫይረስ ቀውስ ምክንያት ከ 1.3.20 በኋላ ከስራው የተባረረ ወይንም ያለ ክፍያ ለዕረፍት የወጣ ማንኛውም ሰው በሚከተሉት መስፈርቶች መሠረት ይህን እርዳታ መቀበል ይችላል፡፡
በሚቀጥሉት ቀናት እርዳታውን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ መመሪያዎችን እናስታውቃለን፡፡
ለክፍያው ብቁነት መስፈርቶች፦
1. እርስዎ የእስራኤል ነዋሪ መሆን
2. እድሜዎ 67 ወይም ከዚያ በላይ
3. ከስራዎ ከመባረርዎ በፊት ወይንም ያለ ክፍያ ለዕረፍት ከመውጣትዎ በፊት ቢያንሥ ለ 3 ወራት ያህል ከሰሩ፡፡
4. በኮሮና ቫይረስ ቀውስ ምክንያት ቢያንስ ለ 30 ቀናት መሥራት ካቆሙ፡፡
የልገሳው መጠን፦
እርዳታው የሚከፈለው ከጡረታዎ በሚከፈለው ገቢ መሠረት ነው (የአዛውንት ዜጋ ክፍያ ለልገሳው ክፍያ ለማስላት ከግምት ውስጥ አይገቡም)።
ለመጋቢት ወር የልገሳ ክፍያ፦
በኮሮና ቫይረስ ቀውስ ምክንያት ከ 1.3.20 በኋላ ከስራው የተባረረ ወይንም ያለ ክፍያ ለዕረፍት የወጣ ማንኛውም ሰው፤ በጡረታ ገቢው መሠረት ለመጋቢት ወር የሚሰጠውን የልገሳ ክፍያ መቀበል ይችላል፡፡
- የ 2,000 ሸኬል ድጎማ - የጡረታ ገቢው ከ 2,000 በታች ለሆኑ ወይም የጡረታ ገቢ ለሌላቸው ይሰጣል።
- የ 1,500 ሸኬል ድጎማ - የጡረታ ገቢው ከ 2,000_4,000 ሸኬል ገቢው ለሆነ ሰው ይሰጣል፡፡
- የ 1,000 ሸኬል ድጎማ - የጡረታ ገቢው ከ 4,000_5,000 ሸኬል ገቢው ለሆነ ሰው ይሰጣል፡፡
ለሚያዚያ ወር የልገሳ ክፍያ፦
በመጋቢት ወር የልገሳው ክፍያ ብቁ ሆነ ከተገኘ እና ወደ ሥራ እስከ 19.4.20 ቀን ድረስ ወደ ስራ ካልተመለሰ ወይንም ከሥራ የተባረረ ወይንም ያለ ክፍያ ለእረፍት እስከ 19.4.20 የወጣ ሰው፤ በሚያዚያ ወር ለሚሰጠው ልገሳ በጡረታ ገቢው መሠረት ለመቀበል ብቁ ይሆናል፡፡
- የ 4,000 ሸኬል ድጎማ-የጡረታ ገቢው ከ 2,000 በታች ለሆኑ ወይም የጡረታ ገቢ ለሌላቸው ይሰጣል።
- የ 3,000 ሸኬል ድጎማ - የጡረታ ገቢው ከ 2,000_3,000 ሸኬል ለሆነ ሰው ይሰጣል፡፡
- የ 2,000 ሸኬል ድጎማ - የጡረታ ገቢው ከ 3,000_4,000 ሸኬል ለሆነ ሰው ይሰጣል፡፡
- የ 1,000 ሸኬል ድጎማ - የጡረታ ገቢው ከ 4,000_5,000 ሸኬል ለሆነ ሰው ይሰጣል፡፡
የአዛውንት ዜጋ ክፍያ እና የገቢ
መደጎሚያ ክፍያ የሚቀብሉ አዛውንቶች ልብ ማድረገ ያለባቸው ነገሮች፦
የተቀበሉት ልገሳ፤ ከገቢ መደጎሚያው ክፍያ ጋር ለሚቀበሉት ክፍያ አብሮ እንዲታሰብ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ግን በልገሳው ምክንያት የገቢ መደጎሚያ ለመቀበል ብቁ ሆነው ካልተገኙ፤ ከሌሎች ተቋማት ጋር የተቆራኙትን ክፍያዎች እንደሚቀበሉ ሊያውቁ ይገባል፡፡
በቤት ውስጥ ለሚሰሩ ሠራተኞች የሥራ አጥነት ክፍያዎች፦ የብቁነት መገምገሚያ ሁኔታዎች መሰረት ነው
በኮሮና ቫይረስ ቀውስ ምክንያት ስራቸውን ለማቆም የተገደዱት የቤት ሠራተኞች የሥራ አጥነት ክፍያ ለመቀበል ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁነት ለመሆን፤ ለክፍያው
የብቁነትመገምገሚያሁኔታዎች መሠረት ነው::
የቤት ሰራተኞች ለሁለት ሳምንት ለብቻቸው ተገልለው ከቆዩ ወይም ፈረቃቸው ከተቀነሰ፤ ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁ አይደሉም ፡፡
በቤተሰብ ውስጥ ለሚሰሩ የሥራ ዓይነቶች፦ ከዚህ ይጫኑ፡፡
ስድስት ወር ለሰሩ ሠራተኞች የሥራ አጥነት ክፍያ፦
ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁ ለመሆን ከሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ የስራ የብቃት ሚዛን ማከማቸት ነው፡፡
ካለፉት 18 ወራት ተቀጣሪ ሆኖ ቢያንስ ለ 12 ወራት በደመወዝ ከሰራ- የስራ አጥነት ክፍያውን ለመቀበል ብቁ ነው፡፡ ለብቃት ሚዛን ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉ ተጨማሪ የሥራ ወራት አሉ፡፡
ጊዜያዊ የድጎማ ክፍያ ለሚቀብሉ እና ክፍያውን ለመቀብል ጊዜውን ለማራዘም
በኮረና ቫይረስ ምክንያት ጊዜያዊ የድጎማ ክፋያ ለሚቀበሉ ሰዎች፤ ለክፍያ ብቁነት እንዲሆኑ እኛ ጊዜን እናራዝምላቸዋለን፡፡
- የአዛውንት እንክብካቤ ክፍያ ተቀባዮች፦ እስከ መጋቢት ወር መጨረሻ ክፍያውን በጊዜያዊ ለመቀበል ብቁ መሆናቸው የተወሰነላቸው ሰዎች፤ የመቀበል ብቁነታቸው እስከ 31.5.2020 ድረስ ይራዘምላቸዋል፡፡
-
የአካል ጉዳት የጡረታ ተቀባዮች፦ ፣ የአካል ጉዳተኛ ሕፃን ፣ ልዩ አገልግሎቶች - የክፍያው ብቁነታቸው የሚጠናቀቀው በመጋቢት፣ ሚያዚያ ወይንም ግንቦት ወር ግማሽ ላይ ሲሆን፤ ወደፊት ለሚመጡት አራት ወራት እንዲቀበሉ ተወስኗል፡፡
-
የሥራ አካል ጉዳተኞች ጡረታ ተቀባዮች፦ ለጡረታ ብቁነታቸው እስከ 30.6.2020 ድረስ ተራዝሟል፡፡
- የጥላቻ ሰለባዎች ተቀባዮች፦ ለጡረታ ብቁነታቸው በ 3 ወሮች ይራዘማል ፡፡
ከቢቱዋህ ሌኡሚ የመቀበል ብቁነታቸው የተራዘመላቸው ሰዎች መልዕክት ወደ ቤታቸው ይላክላቸዋል፡፡
የህክምና ኮሚቴዎችን መፈፀም፦
እንደተለመደው የህክምና ኮሚቴዎችን ማሰባሰብ አስቸገሪ በመሆኑ እና በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መመሪያዎች መሠረት የኮሚቴዎች እንዲሰበሰቡ ስለማይፈቅድላቸው፤ እኛ ያለ አመልካቾች የህክምናውን ዶክሜንቶች አማካይነት ማመልከቻቸውን እንፈትሻለን፡፡ ይህም ለአመልካቾች የክፍያ ብቁነታቸውን ለመወሰን ነው፡፡
በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የኮሚቴው ሀኪም የይገባኛል ምክንያቶችን ለመስማት ሲባል ለአመልካቹ ወይንም እርሱን ለሚወክለው ሰው በስልክ ደውለን እንጠይቃለን፡፡
የይግባኝ ኮሚቴዎች አዲስ መልዕክት እስከሚወጣ ድረስ ተሰርዘዋል፡፡ በእርግጥ ለባለጉዳዮች እናሳውቃለን፡፡
ሀብታሀት ሀክናሳ፦
በኮሮና ቫይረስ ቀውስ ምክንያት ሥራቸውን ለመቀነስ ወይም ለማቋረጥ የተገደዱ፤ በአነስተኛ-ገቢ የሚሰሩ ሰዎች እና የሀብታሀት ሀክናሳ የሚቀበሉ ሰዎች እስከ መጋቢት ድረስ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘታቸውን ይቀጥላል፡፡ ስለሚያዚያ ወር እኛ ወደ ፊት እናሥታውቃለን፡፡
ሲኡድ
በገለልተኛነት ጊዜ የሚገኙ ወይም ብቻውን መሆን ካለበት ሰው ጋር የሚኖሩ የእንክብካቤ አገልግሎት ተቀባዮች በገለልተኛነት ጊዜ እርስዎን መንከባከብ የሚችል ተንከባካቢ ከሌለ፤ ለተንከባካቢው የሚሰጠውን ክፍያ በጥሬ ገንዘብ ሊቀበሉ ይችላሉ
- በዚህሁኔታበሚቀጥለውየመገናኛመረብእኛንያነጋግሩን፡፡
የሕይወት ፍቃድ፦
በዓለም ዙሪያ ባለው የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት በአንዳንድ ሀገሮች በዜጎች እንቅስቃሴ እገዳዎች ምክንያት ወይም በተከሰተው ቀውስ የኮንሱሎች ሥራ መቀነስ ምክንያት የህይወት ፈቃዶችን ማግኘት አስቸጋሪ እንደሆነ እናውቃለን ፡፡
በውጭ አገር የሚኖሩ እና ክፍያውን መቀበላቸውን ለመቀጠል የህይወት ምስክር ወረቀት ማስገባት የሚፈልጉ ሰዎች፤ የህይወት የምስክር ወረቀታቸውን እስከ ሰኔ 2020 ድረስ ሊያቀርቡልን ይችላሉ ፡፡
እስከ ሰኔ ወር ድረስ የህይወት የምስክር ወረቀቶችን ለእኛ ማቅረብ ለሚገባቸው ሰዎች ክፍያውን እንከፍላለን፡፡ (እስከ ሰኔ ወር ድረስ ፈቃዱን የማያቀርብ ማንኛውም ሰው ክፍያው ይቋረጥበታል)።
ይህ ሁኔታ ከቀጠለ፤ የህይወት የምስክር ወረቀት ለማስገባት የተስተካከሉ መመሪያዎችን የያዘ መረጃ ወደ ፊት እናስታውቃለን፡፡
በጥላቻ ለተጎዱት ሰዎች የኅብረት ጉብኝት እና የሙቀት ህክምና
በጥላቻ ጉዳት ለደረሰባቸው የህበረጸቡ አባላት ለተወሰኑ ርዕሰ ጉዳዮች መረጃ፦ የሙቅ መፈወሻ ሕክምና ፣ በሀዘን ምክንያት የቤተሰብ አባሎቻቸውን ከውጭ አገር ማስመጣት እና የሕይወት የምስክር ወረቀቶችን በተመለከተ
ለተጨማሪመረጃከዚህይጫኑ፡፡
የመረጃ እና የድጋፍ ማዕከላት፦
- ብሔራዊ የስልክ ጥሪ ማዕከል፦ በስልክ ቁጥር 6050* ወይንም 04-8812345
-
ብሔራዊመረጃእናየድጋፍማዕከል ለአዛውንት ዜጎች እና ለቤተሰቦቻቸው፦ *9696
-
የእይታእክልላለባቸውሰዎችየቴክኒክድጋፍማዕከል፦ ድህ_ገፁን ከመጠቀም ጋር እርዳታ፤ ድጋፍ ሰጪ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እገዛ እና ድጋፍ ለመቀበል በሚቀጥለው ስልክ ይጠይቁ፦ *5048
ለግል ሰራተኞች እና ነፃ አውጪዎች መመሪያ፦
የስራ አጥነት ክፍያ፦
የግል ሰራተኞች እና ነፃ አውጪዎ ለስራ አጥነት ክፍያ ብቁ አይደሉም፡፡
ሆኖም ግን ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁ ሊሆኑ የሚችሉበት በርካታ የግል ስራ የሚሰሩ ሰራተኞች ሰዎች አሉ፡፡
- መንገድ ገላጭ፦
በዚህየመገናኛመርብሁሉምመረጃተዘርዝሮተቀምጧል፡፡
- በኮሮናን ቫይረስ ምክንያት የስራ ቦታቸው ስራውን ያቆመባቸው መሪዎች(ማድሪሆች)፣ ሌክቸሮች እና መምህራን -
በዚህየመገናኛመርብሁሉምመረጃተዘርዝሮተቀምጧል፡፡
- በኮሮናን ቫይረስ ምክንያት የስራ ቦታቸው ስራውን ያቆመባቸው አርቲስቶች፦
በዚህየመገናኛመርብሁሉምመረጃተዘርዝሮተቀምጧል፡፡
ለግል ተቀጣሪ ሠራተኞች የመጋቢት ወር ክፍያ ለሌላ ጊዜ ተቀይሯል፡፡
በኮሮናን ቫይረስ ምክንያት የመገቢት 2020 የግል ሥራ የሚሰሩ ሰራተኞች ቅድመ ክፍያ ጊዜ ለግንቦት 15 2020 ተቀይሯል፡፡ (ይህም በሚያዚያ 20 ቀን 2020 ፈንታ ነው፡፡)
ቅድመ ክፍያን ማስቀነሥ
በኮሮናን ቫይረስ ቀውስ ምክንያት የተነሳ ገቢያቸው የተቀነሰባቸው የግል ሠራተኞች፤ መግለጫውን ብቻ በመመርኮዝ ለቢቱዋህ ሌኡሚ ቅድመ ክፍያ ለማስቀነስ ቅናሽ ማመልከት ይችላሉ፡፡
ተወካይ ያላቸው የግል ሰራተኞች - ተወካዩ ከቢቱዋህ ሌኡሚ ጋር በተገናኘ የደንበኛ ውክልና ድህረ ገፅ ላይ ማመልከቻውን በማቅረብ ቅድመ ክፍያውን ማስቀነስ ይችላል፡፡
ተወካይ የለላቸው የግል ሰራተኞች - የፈቃድ ሰነዶችን ሳያቀርቡ ቅድመ ክፍያውን
በቅድመማስተካከያ አማካይነት በማመልከት ማስቀንስ ይችላሉ፡፡ ማመልከቻውን ቀጥታ በድርጅቱ
ድህረገፅ በኩል በቀጥታ ለገንዘብ መሰብስቢያ ክፍል መላክ ይችላሉ፡፡
እባክዎን ልብ ይበሉ፦ በዚህ አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ቀድመ ክፍያ ለማስቀነስ ያመለከተ፤ እንደገና ከ 1.4.2020 ጀምሮ ተጨማሪ የቅድመ ክፍያ ቅናሽ ማመልከቻ ማቅረብ ይችላል፡፡
የግል ሰራተኛ ማህደር(ቲክ) መዝጋት
በኮሮና ቫይረስ ቀውስ ምክንያት ለመጨረሻ ጊዜ ሥራቸውን ያቆሙ የግል ሰራተኞች፤ የግል ሰራተኛ ማህደር ለመዝጋት ማመልከቻ ሊያስገቡ ይችላሉ፡፡
የግል ሰራተኛ ማህደር በሚዘጋበት ጊዜ የእነርሱ ቅድመ ክፍያዎች ይሰረዙላቸዋል፡፡ ሰለዚህ በቢቱዋህ ሌኡሚ እነርሱ የግል ሰራተኛ የሚል ማዕረግ የነበራቸው ይሰረዛል፡፡
እባክዎን ያስተውሉ፦ እንደገና በግል ተሰማርተው ለመስራት ከተመለሱበት ቀን ጀመሮ፤ እንደገና በቢቱዋህ ሌኡሚ እንደ አዲሥ መመዝገብ እና
አዲስየግልሰራተኛማህደርመክፈትአለበዎት፡፡ የዚህ አላማም (መብትዎ) እርስዎ እንዳይጎዱ ነው፡፡
ለግል ሰራተኞች የልገሳ ገንዘብ፦
በኮሮና ቫይረስ ቀውስ በኢኮኖሚያዊ ችግር ለተጎዱ ለግል ሰራተኞች መንግሥት የገንዘብ እርዳታ ይሰጣል ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር እና የኢኮኖሚ ሚኒስቴር የእርዳታውን መስፈርቶች እና እንዴት ማመልከት እንደሚቻል ያስታውቃሉ፡፡
ለግል ሠራተኞች - የመጋቢት ወር ክፍያ ማዘግየት (የተለቀቀበት ቀን-መጋቢት 29 ቀን 2020 ዓ/ም)
በኮሮናን ቫይረስ ምክንያት የመገቢት 2020 የግል ሥራ የሚሰሩ ሰራተኞች ቅድመ ክፍያ ጊዜ ለግንቦት 15 ቀን 2020 ዓ/ም ተቀይሯል፡፡ (ይህም በሚያዚያ 20 ቀን 2020 ፈንታ ነው፡፡)
ለሙያዊ ስልጠና ተሳታፊ የሥራ አጥነት ክፍያ፦
በኢኮኖሚ ሚኒስቴር ውስጥ ለሙያ ስልጠና እና የሰው ሀይል ልማት ክፍል የሚሰጠው የሙያ ስልጠና ኮርሶችን በተለያዩ ደረጃዎችና የሙያዎች ዘርፎች ይይዛል፡፡
የሥራ ስምሪት አገልግሎት፤ ስራ ያጡ፣ ሙያ ያልተማሩ ወይም ሙያ ተምረው ነገር ግን ሙያቸው ተፈላጊነት ካልሆነ፤ የስራ እድላቸውን ለማሳደግ ሲባል ወደ ልዩ የሙያ ስልጠና እና አዲስ ሙያ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
በሙያ ስልጠና የሚገኝ ሥራ አጥ ሰው ስልጠና በሚያደርገበት ጊዜ፤ ሳይሰራ ከሚሰጠው የሥራ አጥነት ክፍያ 70% ይሰጠዋል፡፡
ሙሉ የሥራ አጥነት ክፍያ የሚከፈለበት ሙያዎች፦
ከኮምፒዩውተር ጋር ግንኙነት ያሉትን ነገሮች ማቀነባበር፡፡
ሞዴሎችን እና ፈጠራዎችን መስራት
የመሰረት ሙያዎች ፣ ጥሩ የግንባታ እና የኢንዱስትሪ ግንባታ
ማሽኖች ማሰራት፣ የመሳሪያዎች እና ሻጋታዎች ግንባታ - በብረት ወይም በፕላስቲኮች ውስጥ ልዩ ሙያ መካን፡፡
ጨርቃ ጨርቅ ስራ፡- የሽመና ፣ የመቅቢያ፣ ማከሚያ ማሽኖች ማሰራት፡፡
ባህላዊ የምግብ ማብሰል
• ኤሌክትሮኒክስ ፣ ሜካኒካል ፣ ኤሌክትሪክ እና የምህንድስና ሜካኒካል ቁሶን ማሰራት
የግብርና ሜካናይዜሽን ፣ የእርሻ ሥራ አያያዝ
ለእርዳታ መሰልጠን
የኤሌክትሮኒክስ ማምረቻ ሠራተኞች
የሥራ አጥነት ክፍያ በሙያ ስልጠና በመሳተፍ ላይ የሚገኝ አንድ ሰው፤ የስራ አጥነት ክፍያ ስልጠናውን በሚወስድ ጊዜ የመቀበል መብት አለው፡፡ ነገር ግን
ከሚፈቀደውየስራአጥነትቀናት ሳይበልጥ መሆን አለበት፡፡
አንድ ሰው ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁ ሊሆን የሚችለው፤ የትምህርት ደርጃው የ 12ኛ ክፍል ትምህርት ያላጠናቀቀ ከሆነ፤ የሙያ ሥልጠና ትምህርት ውስጥ የሚሳተፍ እንደመሆኑ መጠን በእሱ ምክንያት ከሚፈቀደው ከፍተኛ የሥራ አጥነት ቀናት በሚበልጥ ጊዜ ውስጥ የሥራ አጥነት ክፍያ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡ ነገር ግን ከ 138 ቀናት አይበልጥም፡፡
ለጦር ኃይል፤ ሽሩት ሌኡሚ እና ለዜጎች በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለጨረሱ ወጣቶች የሥራ አጥነት ክፍያ፦
ለጦር ኃይል፤ ሽሩት ሌኡሚ እና ለዜጎች በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ወቅት ለስራ አጥነት ክፍያ ብቁ አይደሉም፡፡
ለመደበኛ የወትድርና አገልግሎት ለጨረሱ ወጣቶች የሥራ አጥነት ክፍያ፦
መደበኛ የወትድርና አገልግሎት የጨረሰ ወጣት እንደማንኛውም ስራ አጥ ሰው፤ የስራ አጥነት ክፍያ ለማግኘት
መስፈርቶችንማሟላት ያስፈልጋል፡፡
- የሥራ አጥነት ክፍያ ለመቀበል በሥራ ስምሪት አገልግሎት መስሪያ ቤት መገኘት ያስፈልጋል፡፡
- እንደ ማንኛውም ሥራ አጥነት ከስራ ስምሪት አገልግሎት መስሪያ ቤት ከመምጣትዎ በፊት ካለፉት 18 ወራት ውስጥ፤ 12 ወራት ስራ ምስራት ያስፈልገግዎታል፡፡ ለብቃት መመዘኛ ከፍተኛው የወራት ብዛት፤
ከመደበኛ የውትድርና አገልግሎት 6 ወራት ብቻ ግምት ውስጥ መግባት ይችላሉ።
ከመደበኛ አገልግሎት በሚለቀቁበት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ አጥነት ሁኔታ ከጀምሩ፤ ለሥራ አጥነት ክፍያ የሚቀበሉት
ከፍተኛየቀንብዛት _70 ቀናት ናቸው፡፡
የሚቀበሉት
ሥራአጥነትክፍያመጠን የሥራ አጥነት ጊዜ ሳይጀምሩ ሲቀበሉት የነበረውን ደመወዝ መጠን ተመርኩዞ ይሰላል፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ከውትድርና አገልግሎት ለተለቀቀ ወታደር ህግ መሰረት ከ 120 ሸቄል በታች ለቀን አያንሥም፡፡
በሥራ ስምሪት አገልግሎት አማካይነት የሙያ ስልጠና፦
ከመደበኛ አገልግሎት በሚለቀቁበት የመጀመሪያ ዓመት የሙያ ስልጠና ከጀመሩ፤ የሥራ አጥነት ክፍያ ለመቀበል
የስራ ብቃት መመዘኛ ጊዜ አያስፈልግዎትም። እንዲሁም በሙያ ስልጠና ለመከታተል በተለቀቁበት የመጀመሪያ አመት ከስራዎ ከተሰናበቱ፤ ለስራዎ መልቀቅ ትክክለኛ ምክንያት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡
ከመደበኛ አገልግሎት በሚለቀቁበት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ አጥነት ሁኔታ ከጀምሩ፤ ለሥራ አጥነት ክፍያ የሚቀበሉት
ከፍተኛየቀንብዛት _70 ቀናት ናቸው፡፡ ነገር ግን የስራ አጥነት ክፍያ ለመቀበል ብቁ ከሆኑ እና የትምህርት ደረጃዎች ከ 12 ዓመት የትምህርት በታች ከሆነ፤ እንዲሁም የሙያ ስልጠና ላይ ከሆኑ፤ ለ 138 ቀናት በትምህርትዎ ጊዜ የስራ አጥነት ክፍያ ይሰጠዋል፡፡
የሚቀበሉት የሥራ አጥነት ክፍያ መጠን፤ የሥራ አጥነት ጊዜ ሳይጀምሩ ሲቀበሉት የነበረውን ደመወዝ መጠን ተመርኩዞ ይሰላል፡፡ በማንኛውም ሁኔታ እንደተወሰነው ከውትድርና አገልግሎት ለተለቀቀ ወታደር ህግ መሰረት ለቀን ከ 84 ሸቄል በታች አያንሥም፡፡
የሥራ አጥነት ክፍያ ለሽሩት ሌኡሚ ወይም ለዜጎች በበጎ ፍቃደኝነት ላገለገሉ ወጣቶች፦
መደበኛ ውትድርና አገልግሎት የጨረሱ ወታደሮች፣ ለዜጎች በብጎ ፍቃድ ላገለገሉ ወይንም ሽሩት ሌኡሚ የጨረሱ ወጣቶች እንደማንኛውም ስራ አጥ ሰው የሥራ አጥነት ክፍያውን ለመቀበል ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡ ስለዚህ ከሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱን የሚያሟሉ ክፍያውን መቀበል ይችላሉ፦
- የ 24 ወራት የሽሩት ሌኡሚ ወይም የዜጎች የበጎ አገልግሎት
- የዜጎች የበጎ አገልግሎት ወይም የሽሩት ሌኡሚ አገልግሎት ቢያንስ ለ 6 ወራት ያገለገለች ሴት እና የአገልግሎት ጊዜው ካበቃ በ 30 ቀናት ውስጥ ከተዳረች
- የዜጎች የበጎ አገልግሎ ወይም ሽሩት ሌኡሚ ለአጭር ጊዜ ያገለገለች፤ እንደ ማንኛውም ዜጋ የሥራ አጥነት ክፍያውን ለመቀበል መስፈርቶችን ማሟላት አለባት፡፡
ከውትድራና በቋሚ ሥራ(ኬቫ) ሲሰሩ የነበሩ እና ያቋረጡ የሥራ አጥነት ክፍያ፦
ከቋሚ ሥራ(ኬቫ) ከተለቀቁ ወዲያውኑ ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
እንደ ሥራ አጥነት ደንብ መሰረት ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁነት ሁኔታዎችን ማሟላት አለብዎት፡፡ ስለዚህ ወደ ሥራ ስምሪት አገልግሎት በመመዝገብ እና እንደማንኛውም ዜጋ ሥራ አጥነት ብቁ ጊዜ ሊኖርዎት ይገባል፡፡
እባክዎን ያስታውሱ፦ የቋሚ ስራ(ኬቫ) አገልግሎት ወራት እንደ ተቀጣሪ ሰራተኛ የሥራ ወራት ይቆጠራሉ፡፡
ማአናክ አቦዳ ንድረሸት(ሞአደፌት)፦
ከመደበኛ የውትድርና አገልግሎት የተለቀቁ እና ሽሩት ሌኡሚ ወይም የዜጎች በብጎ ፍቃድኝነት አገልግሎታቸውን ያጠናቀቁ እና ከተለቀቁ በኋላ ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ አስፈላጊ ስራን(ሞአደፌት) ለ 6 ወር የሰሩ ወጣቶች፤ ከቢቱዋህ ሌኡሚ ልገሳ ለመቀበል መብት አላቸው፡፡
ለተጨማሪመረጃከዚህይጫኑ፡፡የሚሰጠው የገንዘብ መጠን 01.01.2020 ተወስኗል፡፡
ሴቶች ከወለዱ በኋላ የሥራ አጥነት ክፍያ፦
በሥራአጥነትክፍያመስፈርቶች መሠረት ከወለድሽ በኋላ የሥራ አጥነት ክፍያ ለመቀበል ብቁ ልትሆኝ ትችያለሽ፡፡
ማወቅ የሚያስፈልገው፦ ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁ ለመሆን ከሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ በሥራ ስምሪት አገልግሎት መመዝገብ-
ስለምዝገባውተጨማሪመረጃከዚህይጫኑ፡፡
እንዲሁም የወሊድ ክፍያ ከቢቱዋህ ሌኡሚ በሚከፍል ጊዜ የሥራ አጥነት ክፍያ መቀበል አይችሉም፡፡
ሥራዎን የሚያቆሙበት ምክንያት ለስራ አጥነት ክፍያ ብቁነትዎ ተፅኖ ያደርጋል፡፡
ከስራ መሰናበት፦
በወሊድ ክፍያ ጊዜ ውስጥ ወይም በመጨረሻው ጊዜ ከሥራ ከተባረሩ፤ ለስራ አጥነት ክፋይ ብቁ ሊሆኑ የሚችሉት ከተባረሩበት ቀን ወይንም ከወሊድ ክፍያ የመጨረሻ ቀን(ከሁለቱ በኋላ የመጨረሻው ቀን) አንስቶ ነው፡፡ ይህም
በሥራስምሪትአገልግሎትበመጀመሪያበተመዘገቡበትቀንመሰረትይሆናል፡፡
እባክዎን ያስተውሉ፦ አንድ አሠሪ በወሊድ እረፍት ላይ ያለችን እናት የወሊድ እርፍት ጊዜዋን ብጨርስም፤ እስከ 60 ቀናት በሴቶች የስራ ህግ መሰረት ሊያባራት አይችልም፡፡
በወሊድ ምክንያት ከስራ መሰናበት፦
ከወለዱ በኋላ በፍቃደኝነት ሥራዎትን ያለ በቂ ምክንያት ካቆሙ፤ ስራዎን ከለቀቁ ከ 90 ቀናት በኋል ነው የስራ አጥነት ክፋያ ማግኘት የሚችሉት፡፡ ይህም
በሥራስምሪትአገልግሎትበመጀመሪያበተመዘገቡበትቀንመሰረትይሆናል፡፡
ከአሰሪዎ በትክክል መስራት ያቆሞበት ቀን የተፃፈበት ፍቃድ ማምጣት ያስፈልገዎታል፡፡
ስራዎን የለቀቁበት አሳማኝ ምክንያት ካለዎት - ለ 90 የሥራ ቀናት ሳይጠብቁ ከስራዋ እንደተሰናበተች ሴት ሥራ አጥነት ክፍያውን ለመቀበል ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ለሥራ መልቀቂያ ምክንያት ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርበዎታል፡፡
ከወሊድ በኋላ ትክክለኛ የስራ መሰናበቻ ምክንያቶች፦
-
ተቀባይነት የለለው የሥራ ሰዓቶች፡- በርካታ የስራ ሰዓታት (በቀን ከ 8 ሰዓታት በላይ) ወይም የፈረቃ ሥራ ወይም የክፍፍል ስራ።
-
የሥራ ቦታ ርቀት፡- በሥራ ቦታዎ እና በሚኖሩበት ቦታ መካከል ያለው ርቀት ከ 40 ኪ.ሜ. በላይ ወይም ወደ እርስዎ የሥራ ቦታ መደበኛ የሕዝብ መጓጓዣ ከለለ፡፡
-
የእናትነት ሥራ አለመኖር - የሴት ሠራተኞች ሕግ መሠረት አሠሪዎ እንደ እናት ሊቀጥሩዎ(ሚስራት ኤም)ካልቻለ ወይንም ካልፈልገ፡፡
-
ሁኔታዎችን ማክፋት፡- አሰሪው ከመውለድዎ በፊት ከሠሩበት ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር፤ አሁን በሥራዎ ላይ ጫና የሚያደርግ ከሆነ፡፡
-
የጤና ሁኔታ - በጤናዎ ሁኔታ ወይም በቤተሰብዎ አባል (አንድ ወላጅ፣ የትዳር ጓደኛ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ፣ ወንድም ወይም እህት)
እባክዎን ልብ ይበሉ፦ በቢቱዋህ ሌኡሚ ህግ መሠረት መውለድ ለሥራ መልቀቂያ ትክክለኛ ምክንያት አይደልም፡፡
ከወሊድ በኋላ ያለ ክፍያ እረፍት፦
የወሊድ ክፍያ ጊዜ ካለቀ በኋላ ከመውለድዎ በፊት ከሠሩባቸው የወራት ብዛት እስከ አንድ አራተኛ ያህል ድረስ ከስራዎ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡
ይህ ጊዜ ክፍያ ሳይከፈለዎ እንደሚወሰድ እረፍት ይቆጠራል፡፡
ያለ ክፍያ እረፍት በነበሩበት ጊዜ ለስራ አጥነት ክፍያ ማመልከቻ አስገብተው ከሆነ፤ እኛ አሠሪዎን ወደ ስራ ሲመለሱ ተቀብለዎት ማሰራት እንደሚችል እንጠይቀዋለን፦
- አሠሪዎ ወደ ስራ መመለስ የማይችል ከሆነ፤ የሥራ አጥነት ክፍያ ለመቀብል ያመልከቱ ማመልከቻ ይፈቀዳል፡፡ ማመልከቻዎ የሚፈቀደው የስራ አጥነት መስፈርቶችን አሟልተው ሲገኙ ይሆናል፡፡
- አሠሪው ወደ ሥራ ሊመልስዎ የሚችል ከሆነ፤ ነገር ግን እርስዎ ለመመለስ ዝግጁ ካልሆኑ፤ እንደስራ አጥ ሰው ስለማይቆጠሩ ያስገቡት ማመልከቻ መልሱ አውንታዊ ይሆናል፡፡
እባክዎን ያስተውሉ፦ ከላይ እንደተጠቀሰው ያለ ክፍያ ለእረፍት ከወጡ፤ ከዚህ ቀን ጀመሮ የስራ አጥነት ክፍያ ሊቀበሉ ይችላሉ፡፡ ይህም
በሥራስምሪትአገልግሎትበመጀመሪያበተመዘገቡበትቀንመሰረትይሆናል፡፡
ከቢቱዋህ ሌኡሚ ተጨማሪ ክፍያ ተቀባዮች፦
ከሚከተሉት ክፍያዎች ውስጥ አንዱን የሚቀበለው ሥራ የሌለው ሰው በተመሳሳይ ጊዜ የሥራ አጥነት ክፍያ መቀበል አይችልም፦
- በሥራ ላይ በተከሰተ አደጋ ምክንያት የአካል ጉዳተኛ ክፍያ
- የእርግዝና ጥበቃ(ሽሚራ)ክፍያ
- የወሊድ ክፍያ
- በሚሉኢም ለሚየገለግሉ ክፍያ - ሚሉኢም የሚየገለግሉ ሰዎች ክፍያ ቢያንስ በሚሉኢም ባይሆን ኖሮ የሚያገኘው የሥራ አጥነት ክፍያ መጠን ያህል ይሆናል፡፡ ሚሉኢም የሚያገለግል ለስራ ስምሪት አገልግሎት ማስታወቅ አለበት፡፡ ምክንያቱም በውትድራ እያለ እንደስራ አጥ እንዳይመዘግቡት፡፡
- ለሥራ አጥነት ክፍያ እና በተመሳሳይ ጊዜ ለአዛውንት ዜጋ ክፍያ ለመቀበል መብት ያላት ሴት፤ ከሁለቱ ከፍተኛ መጠን ያለውን ክፍያ ትቀበላለች፡፡
ከአንድ በላይ የቢቱዋህ ሌኡሚ ክፋያ ለመቀበል ብቁነት ሁኔታዎችን ካሟሉ፡-
ሁለቱንበተመሳሳይጊዜሊቀበሉየሚችሉመሆኑንወይምከሁለቱአንዱንለመቀበልበሚቀጥለውማስያአማካይነትማጣራትይችላሉ፡፡
ሥራ አጥነት - የኮሮና ቫይረስ ቀውስ ምክንያት የሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶች፦
-
በኮሮናቫይረስቀውስምክንያትቀጣሪዬያለክፍያእረፍትአስወጣኝ፡፡የሥራአጥነትክፍያመቀበልእችላለሁወይ?
-
ለ 30 ቀናት ወይም ከዚያ በላይ ያለ ክፍያ ለእረፍት ጊዜ ከወጣ እና ለዚህ ብቁ ሆኖ ከተገኘ የሥራ አጥነት ክፍያ መቀበል ይችላል፡፡
-
የሥራ አጥነት ክፍያ ለመቀበል የሚፈለግበትን የብቃት ጊዜ የለለው እና ገቢ የሌለው ወይም ገቢው ዝቅተኛ ከሆነ -
ለሀብታሀትሀክናሳ ድጓሜ ብቁነቱን ይጠይቅ፡፡
-
ማንኛውም የጡረታ ዕድሜው የደረሰ እና ለሥራ አጥነት ክፍያ መብት የሌለው - ለአዛውንት ዜጋ ክፍያ ብቁ መሆኑን ይጠይቅ፡፡ እንዲሁም ገቢው ዝቅተኛ ከሆነ ለአዛውንት ዜጋ ክፍያ ተጨማሪ የገቢ ድጓሜ የማግኘት መብቱን ይጠይቅ፡፡
-
አሠሪዬኩባንያውንዘግቶሁሉንምሠራተኞችንአባረረ፣የሥራአጥነትክፍያየመቀበልመብትአለኝ?
ከሥራ የተባረሩ ሠራተኞች የሥራ አጥነት ክፍያ በማግኘት ይችላሉ፡፡ ይህ የሚሆነው የሥራ አጥነት ክፍያ
ብቁነትመስፈርቶችንሲያሟሉነው፡፡
የሥራ አጥነት ክፍያ ለመቀበል የሚያስፈልገውን የጊዜ ብቃት ያላሟላ እና ገቢ ከሌለው ወይም ገቢው ዝቅተኛ ከሆነ
- ለሀብታሀትሀክናሳ ድጓሜ ብቁነቱን ይጠይቅ፡፡
ማንኛውም የጡረታ ዕድሜው የደረሰ እና ለሥራ አጥነት ክፍያ መብት የሌለው - ለአዛውንት ዜጋ ክፍያ ብቁ መሆኑን ይጠይቅ፡፡ እንዲሁም ገቢው ዝቅተኛ ከሆነ_
- ለሀብታሀትሀክናሳ ድጓሜ ብቁነቱን ይጠይቅ፡፡ -
ከስራተባረሩኩኝ፡፡ የሥራአጥነትክፍያለማግኘትምንማድረግአለብኝ?
- ማድረግ ያለብዎት ነገሮች፦
በሥራ ስምሪት አገልግሎ ምዝገባ - ስራዎን እንዳቋረጡ በሥራ ስምሪት አገልግሎት ወዲያውኑ መመዝገብ አለብዎት፡፡ በስራ ስምሪት አገልግሎት
ድህረ_ገፅመመዝገብ ይችላሉ ፡፡ ከተመዘገቡ በኋላ በስራ ስምሪት አገልግሎት ማዕከላት ውስጥ በአካል መገኘት ስለለበዎት ሁኔታ መመሪያዎችን መከተል ያስፈልጋል፡፡ -
የሥራ አጥነት ክፍያ መጠየቅ፡- የስራ አጥነት ክፍያ ማመልከቻዎችን በአጭር መልስ ለመስጠት፤ በድህረ_ገፃችን ማመልከቻዎን እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን፡፡ ከማመልከቻዎ ጋር መቅረብ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን መረጃ ለማወቅ
ከዚህይጫኑ፡፡
-
በስራስምሪትአገልግሎትውስጥተመዝገቤያለሁ፦ ለቢቱዋህሌኡሚማምልከቻማስገባትያለብኝበስንትጊዜውስጥነው?
በሥራ ስምሪት አገልግሎት ከተመዘገቡ፤ የርስዎ መብቶች በቢቱዋህ ሌኡሚ ይጠበቃሉ፡፡
ማለትም የሥራ አጥነት ክፍያ ለቢቱዋህ ሌኡሚ ለማቅረብ መጨነቅ አይገባዎትም፡፡ ከአሠሪው ዘንድ ፍቃዱን ለማግኘት ጥቂት ተጨማሪ ቀናት ካስፈለገው ችግር የለም፡፡
-
የሥራአጥነትክፍያመጠንእንዴትይሰላል?
የሥራ አጥነት ክፍያ መጠን የመጀመሪያ በሥራ ስምሪት አገልግሎት ከመመዝገብዎ በፊት ባሉት 6 የስራ ወራት በተቀበሉት የደመወዝ መጠን እና በእድሜዎ መሰረት ነው፡፡
በደመወዝዎ ላይ የተመሠረተ ፈጣን እና ቀላል የሥራ አጥነት ክፍያ ስሌትን ለማግኘት ወደ
ሥራአጥነትክፍያማስያ ይግቡ፡፡
ስለ ክፍያው መጠን ለተጨማሪ መረጃ
ከዚህይጫኑ፡፡ -
በሥራስምሪትቢሮየመጀመሪያምዝገባከተመዘገብኩበኋላምንማድረግይኖርብኛል?
ከመጀመሪያው የሥራ ስምሪት ምዝገባ በኋላ ለቢቱዋህ ሌኡሚ የሥራ አጥነት ክፍያ ማመልከቻ ማስገባት አለብዎት፡፡
የሥራ አጥነት ክፍያ መጠየቅ፡- የስራ አጥነት ክፍያ ማመልከዎችን በአጭር መልስ ለመስጠት፤ በድህረ_ገፃችን ማመልከቻዎን እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን፡፡ ከማመልከቻዎ ጋር መቅረብ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን መረጃ ለማወቅ
ከዚህይጫኑ፡፡ -
ለስራአጥነትክፍያያቀረብኩትማመልከቻእየታየእንደሆነእንዴትማወቅእችላለሁ?
ማመልከቻውን በድህረ_ገፅ ላይ ለመከታተል እንዲችሉ፤ በግል የመገናኛ መረቦች አገልግሎት በደህረ_ገፃችን እንዲመዘገቡ እንጋብዘወታለን። -
ከሁለትአሠሪዎችእሠራለሁ፡፡ አንደኛው አሠሪያለክፍያለእረፍትአስወጣኝ፡፡የሥራአጥነትክፍያውንመቀበልእቻላልሁወይ?
ለስራ አጥነት ክፍያ ብቁ የሚሆኑት ለ 30 ቀናት ያለ ክፍያ እረፍት ለመውጣት ከተገደዱ እና ለዚህ ክፍያ ለመቀበል መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሆነ ነው፡፡ ስለዚህ በስራ ስምሪት አገልግሎት ድህረ_ገፅ ላይ መመዝገብ እና የስራ አጥነት ክፍያ ለመቀብል ከሁሉም አሰሪዎ የደመወዝ ፋቃድ በመጨመር ማመልከቻዎን በድህረ_ገፁ ያቅርቡ፡፡
ከማመልከቻዎ ጋር መቅረብ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን መረጃ ለማወቅ
ከዚህይጫኑ፡፡
-
ያለፈውዓመትየሥራአጥነትክፍያተቀብየነበር፡፡አሁንወደሥራእንደተመለስኩ፤አሰሪዬያለክፍያእረፍትአስወጣኝ፡፡የስራአጥነትክፍያመቀበልእችላለሁወይ?
ሁሉንም የሥራ አጥ ቀናትዎን ካልተጠቀሙ፤ ስለ ቀሪ የሥራ አጥ ቀናትዎን ተመልሰው ክፍያውን መቀበል ይችላሉ፡፡ ለሥራ አጥነት ክፍያ ሌላ ማመልከቻ ማቅረብ አያስፈልግዎትም፡፡
ስራስምሪትአገልግሎትድህረ_ገፅብቻይመዝገቡ፡፡
ከመጋቢት 1.3.20 በኋላ የሥራ አጥነት ቀናት ካለቀብዎት፤ እርስዎ ሳያመለክቱ እኛ እስከ ሚያዚያ 30.4.20 የስራ አጥነትዎን ክፍያ እናራዝመውለታለን፡፡
እባክዎን ያስተውሉ፦ ለስራ አጥነት ክፍያ ብቁ ለመሆን፤ ያለ ክፍያ እርፈት የወጡት ለ 30 ቀናት ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ ነው፡፡ -
እድሜዬ 68 ዓመትነው፡፡ አሠሪዬያለክፍያለእረፍትአስወጥቶኛል፡፡የሥራአጥነትክፍያ መቀበልእችላለሁን?
የሥራ አጥነት ክፍያ የሚሰጠው እስከ ጡረታ ዕድሜ ድረስ ማለትም እስከ 67 ዓመት ድረስ ነው፡፡
በዚህ ሁኔታ
ለአዛውንትዜጋ ክፍያ ብቁ መሆንዎን ማረጋገጥ እና ገቢዎት ዝቅተኛ ከሆነ፤ እንዲሁም ለአዛውንት ዜጋ ክፍያ
ተጨማሪየገቢመደጎሚያ ብቁ መሆንዎን ማረጋገጥ ያስፈልገዎታል፡፡
የኮሮናን ቫይረስ ቀውስ ምክንያት የ67 ዓመት ዕድሜ አዛውንቶች (ሴቶችንና ወንዶችን) ስራ መስራት ካቋረጡ፤ ለልዩ ልገሳ ብቁ ሊሆን ይችላሉ፡፡
የብቁነት መስፈርቶችንእናየእርዳታውንመጠንለማወቅከዚህይጫኑ፡፡
-
ያለክፍያእረፍትአስወጥተውኛል፡፡ በእረፍቱመጨረሻወደስራለመመለስእቅድአለኝ፡፡በስራስምሪትአገልግሎትውስጥመመዝገብያስፈልገኛል?
አዎ ፡፡ ያለ ክፍያ ለዕርፈት ከወጣ ወይም ከተባረረ ማንኛውም በስራ ስምሪት አገልግሎት ውስጥ መመዝገብ እና በተመሳሳይ ጊዜ ለስራ አጥነት ክፍያ ለመቀበል ብቁ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡
በስራ ምሪት አገልግሎት ምዝገባ መሠረት የሥራ አጥነት ክፍያውን እንከፍላለን፡፡ ስለሆነም ሥራ እንዳቆሙ ወዲያውኑ በስራ ስምሪት አገልግሎት መመዝገብ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ ድርጅት ድህረ_ገፅ ላይ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ -
የሥራዬመጠንተቀንሶብኛል፡፡የሥራአጥነትክፍያማግኘትእችላለሁን?
አይ. የሥራ አጥነት ክፍያ ከስራ ለተባረሩ ወይም ስራቸው ለተቋረጠ ሰራተኛ እና እንዲሁም ለ 30 ቀናት ያለ ክፍያ ለዕረፍት ለወጡ ሰራተች ነው የሚከፈለው። -
ከልጆችጋርበቤትውስጥመቆየትስላለብኝ፤ ወደሥራመሄድአልችልም፡፡ የሥራአጥነትክፍያ መቀበልእችላለሁን?
አይ. የሥራ አጥነት ክፍያ ከስራ ለተባረሩ ወይም ስራቸው ለተቋረጠ ሰራተኛ እና እንዲሁም ለ 30 ቀናት ያለ ክፍያ ለዕረፍት ለወጡ ሰራተኞች ነው የሚከፈለው። -
ባለፉት 18 ወራትውስጥ 12 የስራወራትንካልሰራሁ፤ ለስራአጥነትክፍያመቀበልእችላለሁ?
ባለፉት 18 ወራት ውስጥ 12 ወራትን ያልሠራ ማንኛውም ሰው እንደ ወታደራዊ አገልግሎት ፣ ሚሉኢም ፣ የወሊድ ክፍያ እና ሌሎችም ባለፉት 18 ወራት ውስጥ ማሟላት ይችላል፡፡ ይህ፣ በሚቀጥለው
የመገናኛመርብተዘርዝሯል፡፡
ያለ ክፍያ ለዕረፍት አሰሪዎ ካስወጣዎ ወይንም ከስራዎ ከ 1.3.20 በኋላ ካባረርዎ እና ካለፉት 18 ወራት ውሥጥ ቢያንስ 6 ወር ከሰሩ፤
ለግማሽየሥራአጥነትክፍያብቁነዎት፡፡ ይህም 12 ወራት ከሰራ ሰው ጋር ሲነፃፀር ነው፡፡
እባክዎን ያስታውሱ፦ የሚሉኢም የአገልግሎት ቀናት ፣ መደበኛ የወትድራና አገልግሎት ጊዜ እና ብሽሩት ሌኡሚ፣ የብጎ ፍቃድ አገልግሎት በ 6 ወር ስልጠና ውስጥ አይቆጠሩም፡፡ -
ለ 14 ቀናትብቻዬንመቆየትአለብኝ፡፡የስራአጥነትክፍያ መቀበልእችላለሁ?
አይ. የሥራ አጥነት ክፍያ ከስራ ለተባረሩ ወይም ስራቸው ለተቋረጠ ሰራተኞ እና እንዲሁም ለ 30 ቀናት ያለ ክፍያ ለእረፍት ለወጡ ሰራተኞች ነው የሚከፈለው። -
እኔየግልሰራተኛነኝ።የስራአጥነትክፍያመቀበልእችላለሁ?
የኮሮናን ቫይረስ ቀውስ ምክንያት የግል ሰራተኛ ለሆኑ ሰዎች የገንዘብ ድጋፍ መስጠት የቢቱዋህ ሌኡሚ ሀላፊነት አይደለም፡፡ የገንዘብ ስጦታውን እና እንዴት ማመልከት እንደሚቻል የገንዘብ ሚኒስቴር እና ኢኮኖሚው ሚኒስቴር ሃላፊነት ነው። -
እኔየዩንቨርስቲተማሪነኝ፡፡በፈረቃእሰራነበር፡፡ነገርግንደመወዜምበጣምዝቅተኛነበር።የሥራአጥነትክፍያእንዴትይሰላልኛል?
የሥራ አጥነት ክፍያ ባለፉት 6 ወራት በተቀበሉት ደመወዝ መሰረት ይሰላል፡፡ ከዝቅተኛው ደመወዝ በታች ከተከፈለዎ (በስራው ድርሻ መስረት) የሥራ አጥነት ክፍያ በትንሹ ደመወዝ ይሰላል፡፡
የሥራአጥነትክፍያለማስላትከዚህይጫኑ፡፡ -
እኔየውጭአገርተቀጣሪነኝ፡፡በአገሬካለውሁኔታእናገለልተኛነትየተነሳያለክፍያለእረፍትአሰሪዬአስወጥቶኛል፡፡ የስራአጥነትንክፍያመቀበልእችላለሁ? ምንማድረግአለብኝ?
ዕረፍቱ ከ 30 ቀናት በላይ ከሆነ ክፍያውን ለመቀብል ብቁ ይሆናሉ፡፡
በስራስምሪትአገልግሎት ድህረ_ገፅ ላይ መመዝገብ እና በድህረ_ገፁ ልዩ መግለጫ መሙላት እና በኢሜል መላክ አለበዎት፡፡(ሁሉም በድህረ_ገፁ ላይ ተዘርዝሯል) ፡፡
በተመሳሳይ ጊዜ በቢቱዋህ ሌኡሚ ድህረ_ገፅ ላይ ለሥራ አጥነት ክፍያ ለመቀበል ማመልከቻ ማቅረብ አለብዎት ፡፡ እንዲሁም በኮምፒዩተር የተሰየመ ቅፅ 100_ ጠቅላላ የእርስዎን ገቢ የሚያሳይ ስለሆነ፤ አሰሪዎ እንደላከልን ማረጋገጥ የእርስዎ ሀላፊነት ነው፡፡ -
እኔመደበኛየውትድርናአገልጋይወታደርነኝ፡፡ እናምከወታደራዊበተሰጠኝየመስሪያፍቃድሠርቻለሁ፡፡አሁንከሥራተባረርኩ።ለስራአጥነትክፍያመቀበልእችላለሁ?
በመደበኛ የውትድርና አገልግሎት ላይ የሚገኝ ወታደር ለስራ አጥነት ክፍያ ብቁ አይደለም ፡፡ -
ቅፅ 100 ምንድንነው?
ቅፅ 100 ከቀጣሪዎ የደመወዝ ክፍያ ማሰባሰቢያ ፎርም ሲሆን በቀጥታ ወደ ቢቱዋህ ሌኡሚ በኮምፒዩተር ሲስተም ይላካል፡፡
አሠሪዎ ቅፅ 100 ማቅረብ አለበት ፡፡ እርሱ በትክክል እንዳደረገው ማረጋገጥ አለብዎት፡፡
-
አሠሪዬያለክፍያለእረፍትአስወጥቶኛል፡፡ነገርግንእኔ ለመኪናየ የግብርቅነሳማድረጉንይቀጥላል፡፡የስራአጥነትክፍያመቀበልእችላለሁ?
ለ 30 ቀናት ወይም ከዚያ በላይ ያለ ክፍያ ለእረፍት የወጣ ማንኛውም ሰው ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁ ሆኖ በመገኘት ክፍያውን መቀበል ይችላል ፡፡
የሚቀበሉት የደመወዝ ሰነዶች በዚህ ጊዜ እንደ ገቢ አይቆጠርም፡፡ -
በቤት ስራ ከብዙአሠሪዎችጋርእሠራነበር፡፡አሁንእነርሱመጥቼእንዳፀዳላቸውአይፈልጉም፡፡የሥራአጥነትክፍያመቀብልእችላለሁ? ምንማድረግአለብኝ?
ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁነት ሁኔታዎችን ካሟሉ የሥራ አጥነት ክፍያ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
ማድረግ ያለብዎት ነገሮች፦
- በስራ ስምሪት አገልግሎት ድህረ_ገፅ መመዝገብ
- የስራ አጥነት ክፍያ ለመቀበል ማመልከቻ በድህረ_ገፁ ያቅርቡ፡፡ እንዲሁም ስራዎን ያቋረጡበትን ምክንያትት ይጥቀሱ፡፡ ከስራ መታገድ
- ሥራ ያቋረጡበት ምክንያቱን በመግለጽ ከአሰሪዎ የሥራ ቅጥር ጊዜ እና ደመወዝ (በለ / 1514) ከሁሉ አሰሪዎች ፍቃድ ከማመልከቻዎ ጋር ያያይዙ፡፡ - ስራዎን ያቋረጡበትን ምክንያት ይግለፁ፦ ሌላ ምክንያት_ የኮሮና ቫይረስ ቀውስ ወይም ቀጣሪው ደብዳቤ ከአሰሪው ፊርማ ጋር ያያይዙ፡፡ እንዲሁም የስራ ማቋረጥ ምክንያት በኮሮና ቫይረስ ቀውስ እነድሆነ ይግልፁ፡፡
ለሥራ አጥነት ክፍያ ብቁነት ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ፡፡
-
አሠሪዬከ 30 ቀናትበላይያለክፍያለዕረፍትአስወጣኝ፡፡የስምንትወርነፍሰጡርነኝ፡፡ 30 ቀናትከማለፋቸውበፊትከወለድኩኝለስራአጥነትክፍያመቀበልእችላለሁ?
ለ 30 ቀናት ወይም ከዚያ በላይ በዕረፍት ከቆዩ የስራ አጥነት ክፍያ ብቁነት መስፈርቶችን የምታሟ ከሆነ፤ ልትቀበል ትችላለች፡፡ ፈቃዱ በመጨረሻ ከ 30 ቀናት በታች ከሆነ፤ በሚፈቀድላቸው የብቃት ሁኔታዎች መሠረት የወሊድ ክፍያ ትቀበላለች፡፡
-
በድህረ_ገፅላይማመልከቻማቅረብግዴታአለብኝ? ማመልከቻውንበእጅማቅረብእችላለሁ?
የተሻለ የሚሆነው ማመልከቻዎን
በድህረ_ገፅ ማቅረብ የተመረጠ ሲሆን፤ ማመልከቻዎን በፍጥነት ተመልክተን ለእርስዎ መልስ ለመስጠት ጊዜ ይቆጥባል። ነገር ግን በዚህ መንገድ(በድህረ_ገፅ) ማመልከቻዎን ማቅረብ ካልቻሉ፤ የጉዳይዎን ማመልከቻ በመሙላት ከቅርንጫፍ ውጭ በሚገኘው የአገልግሎት ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ - ቀደም ሲል ማመልከቻ ካስገባሁእና ሰነዶቼን ማሟላት የሚያስፈልገኝ ከሆነ፤ ምን ማድረግ አለብኝ?
የጎደሉ ሰነዶች ከማብራሪያ ደብዳቤ ጋር ለእኛ መላክ አለብዎት፡፡ ሰነዶቹ በደህረ_ገፃችን በኩል መላክ ይችላሉ፡፡ -
አሠሪዬ እስካሁንሰነዶቹንአልሰጠኝም/ ኩባንያውዝግከሆነ፤ ምንማድረግአለበት?
አይጨነቁ ፣ በስራ ስምሪት አገልግሎት ውስጥ ከተመዘገቡ በቢቱዋህ ሌኡሚ የእርስዎ መብቶች ይጠበቃሉ፡፡ ሁሉም ሰነዶች በእጅዎ ሲሆኑ የስራ አጥነት ማመልከቻዎን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ የሥራ አጥነት ክፍያ በስራ አገልግሎት ከተመዘገቡበት ቀን አንስቶ ይሰጠዎታል፡፡ -
የሥራአጥነትክፍያለመቀበልምንዓይነትሰነዶችን ከማመልከቻውጋርማስገባትአለብኝ?
አሰሪዎ ቅፅ 100 ለእኛ እንደላከልን ማረጋገጥ አለበዎት፡፡ ቅፅ 100_ ጠቅላላ የእርስዎን ገቢ የሚያሳይ ፎርም ነው፡፡
አሰሪዎ ቅፅ 100 ለእና ካላከልን የስራ አጥነት ክፍያ ለመቀበል ወድፊት ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ይህን ቅፅ አሰሪዎ መላክ የማይችል ከሆነ፤ የሥራ ቅጥር ጊዜ እና ደመወዝ (በለ / 1514) ማቅረብ ያሰፈልግዎታል፡፡፡
ወይም ከአሰሪ የሥራ ቅጥር ደብዳቤ - የሥራ ስምሪትዎ መቋረጥ ምክንያትን የሚያመለክቱ (እንደ መባረር ፣ በራስ ሥራ መልቀቅ ፣ ያለ ክፍያ ዕረፍት መውጣት እና ጡረታ መውጣት፣ ወዘተ.) እና የስራዎን ያቋረጡበት ቀን ፣ በአሠሪ ፊርማ የተፈረመበት እና ከ 18 ካለፉት የስራ ወራት የ 12 ወራት ደመወዝ ክፍያ ሰነዶች ከሥራ ስምሪት አገልግሎት ምዝገባ በፊት_የመጨረሻ የ 6 የስራ ወራትን ያጠቃለለ ደብዳቤ ማያያዝ፡፡ -
አንድየዩንቨርስቲተማሪ ለስራአጥነትክፍያብቁነው?
የዩንቨርስቲ ተማሪ እንደማንኛውም ስራ አጥ ሰራተኛ ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ ለስራ አጥነት ክፍያ ብቁነቱ በሁኔታዎች መሠረት ይፈተሻል። -
ሥራአጥነትንክፍያየሚፈቀደለትንቀናትከጨረሰ፤የስራአጥነትቀናትይጨመርለታልወይ?
ከ 1.3.20 በኋላ የሥራ አጥነት ቀናት የጨረሱ ሰዎች፤ የሥራ አጥነት ክፍያቸው እስከ 30.4.20 ድረስ እናራዝምለታለን፡፡
እባክዎ ልብ ይበሉ፦ በቀጥታ እኛ ልናራዝምለት የምንችለው የሥራ አጥነት ዓመታቸውን ላልጨረሱ ሰዎች ይሆናል፡፡(ማለትም ወደ ስራ ስምሪት አገልግሎት ከሄደበት ቀን ጀምሮ አንድ ዓመት ካላለፍ ነው፡፡) ፡፡ የሥራ አጥነት ዓመት ካለፈ አዲስ የሥራ አጥነት ማመልከቻ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡ -
ለ 6 ወራትየስልጠናጊዜያሳለፈሰው፤የሥራአጥነትክፍያ መቀበልይችላል?
ያለ ክፍያ ለዕረፍት አሰሪዎ ካስወጣዎ ወይንም ከስራዎ ከ 1.3.20 በኋላ ከተባረሩ እና ካለፉት 18 ወራት ውሥጥ ቢያንስ 6 ወር ከሰሩ፤
ለግማሽየሥራአጥነትክፍያብቁነዎት፡፡ ይህም 12 ወራት ከሰራ ሰው ጋር ሲነፃፀር ነው፡፡
ማወቅ የሚያስፈልገው ነገር፦
6 የስራ ወራትን ካላስመዘገቡ - በስልጠና ወቅት ሊካተቱ የሚችሉ ተጨማሪ የስራ ወራት ያልሆኑ አሉ_
ለተጨማሪመረጃከዚህይጫኑ፡፡
እባክዎን ያስታውሱ፦ የሚሉኢም የአገልግሎት ቀናት ፣ መደበኛ የውትድራና አገልግሎት ጊዜ እና የሽሩት ሌኡሚ አገልግሎት በ 6 ወር ስልጠና ውስጥ አይቆጠሩም፡፡ -
ከሌላቦታለመስራትየስራቦታዬን ለቀቅሁ፡፡ነገርግንበኮሮና ቫይረስቀውስምክንያትልሰራበትያሰብኩበትአዲሱየሥራ ቦታሥራውንአቁሟል።የሥራአጥነትክፍያውንመቀብልእችላለሁወይ?
ከአዲሱ አሠሪ ጋር የቅጥር ውል ካለዎት የሥራ መልቀቂያዎን እንደ ትክክለኛ የሥራ መልቀቂያ እንቆጥረዋለን፡፡ ስለዚህ የስራ አጥነት ክፍያውን
መቀበያየብቁነትመስፈርቶች መሰረት መቀበል ይችላሉ፡፡ -
አንደተራሰራተኛበራሱ ኩባንያውየሚሰራከሆነእናበተፈጠረውበሁኔታውምክንያትኩባንያውን ለመዝጋትከተገደደየሥራአጥነትክፍያ የማግኘትመብትአለው?
- ትንሽ ኩባንያ (እስከ 5 ባልደረባዎች ያሉት ድርጅት) ከሆነ እና እንደ ባለአክሲዮን ተቆጣጣሪ ተደርጎ የሚቆጠር ከሆነ (ቢያንስ የአክሲዮን ድርሻ 10% ካለው) - ለሥራ አጥነት መብት አያገኙም ፡፡
ስድስት ወይም ከዚያ በላይ አጋሮች ያሉት ኩባንያ ከሆነ - የሥራ አጥነት ክፍያ ለመቀበል ማመልከቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሰራተኛ እና የአሰሪ ግንኙነት መኖሩን እኛ ከፈተሽን በሁሏ የሥራ አጥነት ክፍያው እንደሁኔታው ውሳኔ ይሰጣል፡፡
-
አሠሪዬቅፅ 100 ንከላከ፤ እንዲሁቅጽ 1514 ንማያያዝአስፈላጊነው?
አሰሪዎ ቅጽ 100 ን ከላከልን ቅጽ 1514 (የአሠሪ ማረጋገጫ እና ደመወዝ ቅፅ) መላክ አያስፈልግዎትም፡፡ -
ከኮሮናቫይረስቀውስበፊትሥራአጥነትክፍያአገኝቻለሁ፡፡ ማመልከቻውንካሰገባሁ አንድዓመትገናአልሞላም፡፡አሁንከኮሮናቫይረስቀውስ ምክንያትያለክፍያዕረፍትአስወጡኝ፡፡ የሥራአጥነትክፍያውን ለማግኘትምንማድረግአለብኝ?
ሁሉንም የሥራ አጥነት ቀናትዎን ካልጨረሱ፤ ስለ ቀሪ የሥራ አጥነት ቀናትዎን ተመልሰው ክፍያውን መቀበል ይችላሉ፡፡ ስለዚህ እንደገና አዲስ ማመልከቻ ማስገባት አያስፈልግዎትም፡፡ ማድረግ የሚገባው ነገር፦
ስራስምሪትአገልግሎትድህረ_ገፅብቻይመዝገቡ፡፡
ከመጋቢት 1.3.20 በኋላ ያለ ሥራ አጥነት ቀናት ካለቀብዎት፤ እርስዎ ሳያመለክቱ እኛ እስከ ሚያዚያ 30.4.20 የስራ አጥነትዎን ክፍያ እናራዝምወለታለን፡፡ -
እድሜዬ 63 ሲሆን፤ አሠሪዬ ለ 30 ቀናት ያለ ክፍያ ለዕረፍት አስወጣኝ፡፡ ምን ማድረግ አለብኝ?
የሥራአጥነትክፍያ እና
የአዛውንትዜጋክፍያ ለመቀበል ማመልከቻ ማስገባት አለብዎት፡፡ ስለዚህ ከሁለቱን ከፍተኛውን ክፍያ ለመቀበል ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
በስራስምሪትአገልግሎትድህረ_ገፅ ላይ መመዝገብ እና ለሥራ አጥነት ክፍያ በቢቱዋህ ሌኡሚ ድህረ_ገፅ ላይ ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርብዎታል፡፡ እንዲሁም የደመወዝዎን መረጃ የያዘ አሠሪዎ ቅጽ 100 እንደላከልን ያረጋግጡ፡፡
-
እድሜዬ 68 ዓመትሲሆን፤ አሠሪዬያለክፍያለእረፍትአስወጥቶኛል፡፡የሥራአጥነትክፍያ መቀበልእችላለሁን?
የሥራ አጥነት ክፍያ የሚሰጠው እስከ ጡረታ ዕድሜ ድረስ ማለትም እስከ 67 ዓመት ድረስ ነው፡፡
በዚህ ሁኔታ
ለአዛውንትዜጋ ክፍያ ብቁ መሆንዎን ማረጋገጥ እና ገቢዎት ዝቅተኛ ከሆነ፤ ለአዛውንት ዜጋ ክፍያ
ተጨማሪየገቢመደጎሚያ ማመልከቻ ማስገባት ያስፈልገዎታል፡፡
የኮሮናን ቫይረስ ቀውስ ምክንያት የ67 ዓመት ዕድሜ አዛውንቶች (ሴቶችንና ወንዶችን) ስራ መስራት ካቋረጡ፤ ለልዩ ልገሳ ብቁ ሊሆን ይችላሉ፡፡
የብቁነት መስፈርቶችንእናየእርዳታውንመጠንለማወቅከዚህይጫኑ፡፡ -
የአባቴየግልተንከባካቢብቻዋንመሆነካለባትምንማድረግአለብኝ?
ይህን አገልግሎት ለሚሰጥዎት ኩባንያ ማነጋገር እና ኩባንያው ለአባትዎ ሌላ ተቀያሪ ተንከባካቢ ማግኘት አለበት፡፡ -
አዛውንትአባቴበኮሮናቫይረስምክንያትብቻውንከሆነእናሊንከባከበውየሚችልሰውከሌለ፤ምንማድረግያስፈልጋል?
በገለልተኛነት ጊዜ የሚገኙ ወይም ብቻውን መሆን ካለበት ሰው ጋር የሚኖሩ የእንክብካቤ አገልግሎት ተቀባዮች በገለልተኛነት ጊዜ እርስዎን መንከባከብ የሚችል ተንከባካቢ ከሌለ፤ ለተንከባካቢው የሚሰጠውን ክፍያ በገንዘብ ሊቀበሉ ይችላሉ
- በዚህሁኔታበሚቀጥለውየመገናኛመረብእኛንያነጋግሩን፡፡
የእንክብካቤውን ገንዘብ ክፍያ በስልክ ጥሪ ማዕከል *2637 ይደውሉ ወይም
በድህረ_ገፁ ለእኛ ያመልክቱ፡፡